Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dlcp

dlcp

In observance of the Christmas Holiday, DLCP will be closing at Noon on Tuesday, December 24, 2024, and will remain closed through Wednesday, December 25, 2024. Please see our list of online resources should you need immediate assistance. We will resume normal operations on Thursday, December 26, 2024.

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about the Department of Licensing and Consumer Protection (DLCP) services for Amharic speakers.

የኮሉምቢያ ዲስትሪክት የፍቃድ አሰጣጥና የሸማቾች ጥበቃ መምሪያ (Department of Licensing and Consumer Protection)

የኤጀንሲው ስም፡- የፍቃድ አሰጣጥና የሸማቾች ጥበቃ መምሪያ

የፈቃድ አሰጣጥና የሸማቾች ጥበቃ መምሪያው ተልዕኮ በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ያሉ ነዋሪዎችን፣ የንግድ ድርጅቶችንና ጎብኝዎችን የንግድ እንቅስቃሴዎች ፈቃድ በመስጠትና በመቆጣጠር እንዲሁም የሸማቾች ጥበቃ የአሰራር ሕጎችን በመመርመርና በማስፈጸም ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸውን ማስጠበቅ ነው።

አገልግሎቶች

የፍቃድ አሰጣጥና የሸማቾች ጥበቃ መምሪያው በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት። ኤጀንሲው ሸማቾችን ይጠበቃል፣ የንግድና የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፣ ማኅበራትን ይመዘግባል፣ ለገንዘብ ትርፍ የሚያገለግሉ የመለኪያና የመመዘኛ መሣሪያዎችን ይመረምራል እንዲሁም የልዩ ኹነቶች ፍቃዶችን ይሰጣል።

ክፍሎችና ኃላፊነቶች

የዳይሬክተር ቢሮ

የዳይሬክተሩ ጽ/ቤት ተግባራት የሰው ኃይልን፣ የድጋፍ አገልግሎትን፣ የግዥና የውል አስተዳደርን፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራርን፣ የኤጀንሲውን የፋይናንስ ስራዎችና የመዝገብ አያያዝን ጨምሮ አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን፣ የኤጀንሲው የሥራ አፈፃፀምና የመረጃ አያያዝን፣ የደንበኞች አገልግሎትና የሒሳብ አስተዳደርን፣ የሕግ ጉዳዮችን፣ የሕዝብ ግንኙነቶች እና የመረጃ ቴክኖሎጂን ያካትታሉ፡፡

አስፈጻሚ ቢሮ

የማስፈጸሚያ ቢሮው የፈቃድ አሰጣጥን፣ ሽያጭንና ልዩ ኹነቶችን፣ መለኪያዎችንና መመዘኛዎችን ጨምሮ ሕግን የማይከተሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የማጣራትና የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት። ይህ ቢሮ የሸማቾች ጥበቃን የሚመለከቱ ቅሬታዎችን በሸማቾች ጥበቃ ክፍል በኩል ይመረምራል። ቢሮው የሚከተሉትን ሶስት ተግባራት በሥሩ ይዟል፡-

አስፈጻሚ ክፍል፡- ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመሆን ሁሉንም የሕግ ጥሰቶች ይመለከታል፣ ቅጣቶችን ይሰበስባል እንዲሁም ሌሎች ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡

የሸማቾች ጥበቃ፡- የዲስትሪክቱን ነዋሪዎች በገንዘብ ለመበዝበዝ የሚሞክሩ የንግድ ተግባራትን ይከታተላል። የዲስትሪክቱ ነዋሪዎችና ጎብኝዎች የሸማቾች ጥበቃ መረጃዎችን ማግኘት፣ የንግድ ሥራዎችን ማጥናት፣ ቅሬታ ማቅረብ፣ የዳኝነት አገልግሎቶችን ማግኘት፣ በሕገወጥና ኢ-ፍትሐዊ የንግድ ተግባራት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እንዲመረመሩ መጠየቅ እንዲሁም የሌሎች ደጋፊ ቢሮዎችና ግብዓቶችን ሊንኮች ማግኘት ይችላሉ። ይህ ቢሮ የንግድ ድርጅቶች ተፈጻሚነት ያላቸው የፈቃድ አሰጣጥ፣ የዞን፣ የማኅበራት ውስጠ-ደንብና መመሪያዎችን ተከትለው የሚሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ያለፈቃድ የሚከናወኑ የንግድ ተግባራትን የሚመረምር፣ ለቅሬታዎች ምላሽ የሚሰጥና የንግድ ፈቃድ ማመልከቻዎችን የሚገመግም የቁጥጥር ምርመራን ያካትታል፡፡

ልዩ ኹነቶችና የሽያጭ አስፈጻሚ፡- ልዩ ኹነቶችን እንዲሁም በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችና በመንገድ ላይ የሚሸጡ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ሕግን ተከትለው የሚከናወኑ መሆናቸውን ያረጋግጣል። አስፈጻሚው የህዝብን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከበርካታ የፌደራልና የአካባቢ የመንግስት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር ሥራዎቹን ያከናውናል።

የንግድና የሙያ ፈቃድ አስተዳደር

የንግድ አገልግሎት ማዕከል፡- በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የንግድ ሥራ ለመጀመር፣ ለመመዝገብና ፈቃድ ለሚፈልጉ ነባርና አዳዲስ የንግድ ሥራ ባለቤቶች የስልጠናና የምክር አገልግሎቶችን በመስጠት ደንበኞችን የመርዳት ኃላፊነት አለበት። ይህ ማዕከል ለነባርና አዳዲስ አነስተኛ ንግዶች ተገቢ የማማከር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የኮርፖሬሽን ክፍል፡- በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የንግድ ሥራዎችን የሚያከናውኑ ኮርፖሬሽኖችን፣ ኃላፊነታቸው የተወሰነ ማኅበራትንና የሽርክና ድርጅቶችን የንግድ ስያሜ ምዝገባ ጨምሮ ሁሉንም የሃገር ውስጥ (የዲስትሪክት) ወይም የውጭ (የዲስትሪክት ያልሆኑ) አካላትን የመመዝገብ ኃላፊነት አለበት፡፡

የንግድ ሥራ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ምዝገባ እና እድሳት፡- አዳዲስ የንግድ ፍቃድ ማመልከቻዎችንና የንግድ ፍቃድ እድሳት ማመልከቻዎችን የማከናወን ኃላፊነት አለበት። ይህ የቁጥጥር ተገዢነትን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ለአጭር ጊዜ የኪራይና የልዩ ዝግጅቶች (ለምሳሌ፣ የጎዳና ላይ ፌስቲቫሎች፣ የጤና ትርዒቶች፣ የሰርከስ ትርዒቶች እና በቀጥታ የሚተላለፉ ትርዒቶች) እና በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ለሚከናወኑ ንግዶች (ለምሳሌ፣ የምግብ መሸጫ መኪናዎች፣ የሆትዶግ ጋሪዎች፣ በእግረኛ መንገድ ላይ ሸቀጣ ሸቀጦችን የሚነግዱ ሻጮች እና የአይስክሬም መሸጫ መኪናዎች) ፈቃድ መስጠትን ያካትታል።

የሥራና የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ፡- የዲስትሪክቱን ጤና ነክ ያልሆኑ የሥራና የሙያ ቦርዶችን፣ ኮሚሽኖችንና ፕሮግራሞችን ይደግፋል። ይህ ክፍል ደንቦችን ያስፈጽማል እንዲሁም ከ125 በላይ በሆኑ የሥራና የሙያ ዘርፎች ፍቃድ ይሰጣል። እነዚህ ቦርዶች፣ ኮሚሽኖችና ፕሮግራሞች ማመልከቻዎችን የመገምገም፣ ምርመራዎችን የመምራት፣ በሌሎች አካላት የሚቀርቡ የማረጋገጫ ጥያቄዎችን ምላሽ የመስጠት እንዲሁም የግለሰቦችን የሙያ ተግባራት የመቆጣጠር ኃላፊነት አለባቸው፡፡

የክብደትና መለኪያ መሳሪያዎች፡- በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ለንግድ ተግባር ጥቅም ላይ የሚውሉትን የክብደትና የመለኪያ መሳሪያዎችን የመመርመር ኃላፊነት አለበት።

የትርጉም አገልግሎቶች

በቋንቋዎ እርዳታ ለማግኘት እባክዎን በ(202) 671-4500 ቢሮአችንን ያነጋግሩ። ወደ ቢሮአችን ሲደውሉ ወይም ቢሮአችንን ሲጎበኙ፣ ከአስተርጓሚ ጋር የሚያገናኝዎት ሰራተኛ ያገኛሉ።

 

አድራሻ፡-

The Department of Licensing and Consumer Protection
1100 4th Street SW
Washington, DC 20024
Phone: 202-671-4500
dlcp.dc.gov